lllllllllll primary and middle School
Home Page በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራት በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራት በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ

08th August, 2024

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ከተሰማሩ ዕጩ ተመራቂ ማህበራት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል።

በውይይቱ በዘርፉ የተሰማሩ ማህበራት የማጥራት እና ዕጩ ተመራቂዎች ምልመላ ሂደት ላይ ገለፃ የተደረገ ሲሆን በኮሪደር ልማት ስራ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ማሳደግ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሂዷል።

በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኃላፊ #አቶ መክብብ /ሀና በውይይቱ ማጠቃለያ በሰጡት አስተያየት ከልማዳዊ አሰራር በመውጣት እና ህጋዊ አሰራርን በመከተል በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራት በገበያ ትስስር ብቻ ሳይሆን በከተማዋ እየተከናወኑ ባሉ የተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ ማህበራት በቀጣይ በስድስተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የማሳረፍ መርሀ ግብር ላይ እንደሚሳተፉ አረጋግጠዋል

.

Copyright © All rights reserved.

Created with