lllllllllll primary and middle School
Home Page የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በየደረጃው በሚገኙ የትምህርት ተቋማት ምዘና በማካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በየደረጃው በሚገኙ የትምህርት ተቋማት ምዘና በማካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ።

02nd August, 2024

(ሀምሌ 24/2016 .) ምዘናው የተቋማቱን 2016 . የቁልፍ ውጤት እቅድ አፈጻጸም ጨምሮ የአገልግሎት አሰጣጥ የብልሹ አሰራር እና  ቅንጅታዊ አሰራር አፈጻጸምን መሰረት አድርጎ በመካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን ቀደም ብሎ ምዘናውን ለሚያካሂዱ ባለሙያዎች በምዘናው አካሄድና በመመዘኛ መስፈርቱ ዙሪያ ኦረንቴሽን መሰጠቱ ይታወቃል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ ምዘናው ከትላንት ጀምሮ 11 የክፍለ ከተማ እና 119 ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች እንዲሁም 78 የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካሄዱን ገልጸው ምዘናው በነገው እለትም ቀጥሎ 255 የመንግስት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

ዳይሬክተሩ አያይዘውም ምዘናው በዋናነት በተቋማቱ መካከል ተቀራራቢ አፈጻጸም ተመዝግቦ የትምህርት ልማት ስራውን ውጤታማ ለማድረግ ታስቦ የሚካሄድ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ የምዘናውን ውጤት መሰረት በማድረግ አፈጻጸማቸው ከፍተኛ ለሆነ ተቋማት እውቅና የሚሰጥ መሆኑን አስረድተዋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with